Gesamtlänge aller Episoden: 20 days 17 hours 5 minutes
ዶ/ር ፓስተር ናትናኤል ገመዳ - በዘፀአት የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ፓስተር፤ የፋሲካ በአልን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል ።
ጋዜጠኛና ደራሲ አበራ ለማ፤ በድምፃዊ ጌታቸው ካሣ ተዘፍኖ ዘመን ተሻጋሪ ስለ ሆነው "ሀገሬን አትንኳት" ግጥሙ፣ ስለ ባለ ቅኔ ሎሬየት ፀጋዬ ገብረመድኅን ዘርፈ ብዙ ተጠባቢነትና ወዳጅነት አንስቶ ይናገራል። ሥነ ግጥሞቹንም ያስደምጣል።
ጋዜጠኛና ደራሲ አበራ ለማ፤ በቅርቡ ለአንባቢያን እነሆኝ ስላለው "የዓለማችን ምስጢራት" መፅሐፉና የሥነ ግጥም በረከቶቹ ይናገራል።
ጋዜጠኛና ደራሲ አበራ ለማ፤ የአገረ ኢትዮጵያን የራዲዮ ስርጭት፣ የጋዜጣ ሕትመት ውጤቶችንና የባለ ሙያዎቹን የሥነ ምግባር ደረጃ መዝኖ ግለ አተያዩን ያጋራል።
ከኢትዮጵያ አንጋፋና ስመ ገነን ጋዜጠኞችና ደራሲዎች ውስጥ ቀዳሚ ተጠቃሽ ከሆኑቱ ውስጥ አበራ ለማ አንዱ ነው። በማስታወቂያ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ራዲዮና አዲስ ዘመን ጋዜጣ፣ በግሉ ፕሬስ በአዕምሮ ጋዜጣ የጋዜጠኛነት ድርሻውን አበርክቷል። በድርሰት በረከቶቹም ሰሞነኛውን "የዓለማችን ምስጢራት" መፅሐፉን አክሎ ከ20 በላይ መፅሐፍትን ለተደራሲያን እነሆኝ ብሏል።
The land holds a profound spiritual significance for Aboriginal and Torres Strait Islander peoples, intricately intertwined with their identity, belonging, and way of life. - ለአቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴት ሰዎች መሬት ጥልቅ መንፈሳዊ ፋይዳን የያዘ፣ ከማንነታቸው፣ ውሁድነትና የአኗኗር ዘዬ ጋር ተጋምዶ የተቆራኘ ነው።
ከአፍሪካ ከፍተኛ የኮሌራ ታማሚዎች ቁጥር ኢትዮጵያ ውስጥ መመዝገቡ ተገለጠ
ዶ /ር ለምለም ታምራት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ኮሌጅ የአይን ሀኪም እና የግላኮማ ስቴሽያሊስት (ልዩ ሀኪም ) የአይን ውስጥ እብጠት ግላኮማ ምንም አይነት ምልክቶችን ሳያሳይ እይታችንን ሊጋርድ የሚችል በሽታ ነው ይላሉ።
መጋቢ ሐዲስ ብሩክ ተስፋዬ በሜልበርን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ስብከተ ወንጌል ሀላፊ ፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን አማንያን ዘንድ በተለየ ሁኔታ የሚታሰቡትን የሰሙነ ህማማት ቀናት ትርጓሜ አስረድተዋል ።
በአገረ አውስትራሊያ-ሜልበርን ከተማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤልና የመካነ ሰላም ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤት መዘመራን፤ ቤተልሔም ትዕግስቱ፣ ፅዮን ብሩክ፣ ኤማንዳ ወንድወሰንና ኤፍራታ ሚሊዮን ሰሙነ ሕማማትን ምክን ያት በማድረግ "በጌቴ ሰማኔ" መንፋሳዊ መዝሙርን ያሰማሉ።