Gesamtlänge aller Episoden: 3 days 9 hours 38 minutes
የእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ ዋንጫን ለማንሳት አሁን አሰልጣኝ ሜኬል አርቴታ፤ ዬርገን ክሎፕ እና ፔፕ ጓርዲዮላ ተፋጠዋል ። በመላው አፍሪቃ ጨዋታዎች ውድድር የአስተናጋጇ ሀገር ጋና ጥቋቁር ልዕልታት ሊሲዎችን አሸንፈዋል ። ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ደጊቱ አዝመራው በዙርኪክ ማራቶን ድል ተቀዳጅታለች ። የሻምፒዮንስ ሊግ ፍልሚያ እና ረቡዕ ይኖራል ።
ዳርዊን ኑኔዝ በመጨረሻዎቹ ሰከንዶች ሊቨርፑልን ታድጎ የፕሬሚየር ሊግ መሪነቱን አስጠብቋል ። ፊል ፎደን ማንቸስተር ሲቲ በማንቸስተር ዩናይትድ ላይ የበላይ ሆኖ ድል እንዲቀዳጅ አስችሏል ። ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያዩ የአትሌቲክስ ዘርፎች አሸናፊ ሆነዋል ።
በእንግሊዝ የካራባዎ ዋንጫን ቸልሲ በጉዳት በርካታ ታዳጊዎችን ለማሰለፍ ለተገደደው ሊቨርፑል አሳልፎ ሰጥቷል ። በቱኒዝያ በተከናወነው የአፍሪቃ አገር አቋራች አትሌቲክስ ፉክክር ኢትዮጵያ በሜዳሊያ ሰንጠረዥ የ2ኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች ። ስለ ድሬዳዋ ዓለም አቀፍ ስታዲየም እድሳትና ይዞታ ቃለ መጠይቅ ይኖረናል ።
በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ ሊቨርፑልና አርሰናል ተፋጠዋል ። ማንቸስተር ሲቲተስተካካይ ጨዋታውን ድል አድርጎ ሊቨርፑልን መጣሁልህ ሊለው ጓግቷል ። በጀርመን ቡንደስሊጋ የባዬር ሙይንሽን ሽንፈት ደጋፊዎቹን አስደንግጧል ። የሻምፒዮንስ ሊግ፤ የአውሮጳ ሊግና ኮንፈረስ ሊግ ግጥሚያዎች በቀጣይ ቀናት ይከናወናሉ ። ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ተቀዳጅተዋል ።