Gesamtlänge aller Episoden: 3 days 9 hours 38 minutes
አርሰናል የፕሬሚየር ሊግ ዋንጫ ተፎካካሪነቱን አጠናክሯል ። ሊቨርፑል ዳግም ነጥብ ጥሎ ዋንጫ የማግኘት እድሉን አመንምኗል ። አንድ ተስተካካይ ጨዋታ የሚቀረው ማንቸስተር ሲቲ በግስጋሴው ቀጥሏል ። ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በዓለም መድረክ እንደተለመደው ድል ተቀዳጅተዋል ። የዓለም ክብረወሰን ተሰብሯል፤ በሴትም በወንድም ድሉ የኢትዮጵያ ሆኗል ።
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሮተርዳም ማራቶን ኔዘርላንድስ ውስጥ ድል ተቀዳጅተዋል ። በቤጂንግ የግማሽ ማራቶን የኢትዮጵያ እና የኬንያ አትሌቶችን ቻይናዊው ሯጭ ቀድሞ እንዲገባ ሩጫው ሆን ተብሎ ዝግ ማለቱ መነጋገሪያ ሆኗል ። በጀርመን ቡንደስ ሊጋ ታሪክ ከ120 ዓመት በኋላ ባዬርን ሌቨርኩሰን ለመጀመሪያ ጊዜ ዋንጫ በማንሳት ታሪክ ጽፏል ።
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ትናንት በፈረንሳይ ፓሪስ ማራቶን በወንድም በሴትም ድል ተቀዳጅተዋል ። ከወሳኙ ድል በኋላ አትሌቶቹን አነጋግረናል ። በአውሮጳ ሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ ፍልሚያዎች ነገና ከነገ በስትያ ይከናወናሉ ። በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ ሊቨርፑል በተከላካይ ብርቱ ስህተት ድሉን አሳልፎ ሰጥቷል ። ባየር ሙይንሽንን ዘንድሮ ምን ነካው?
በሰርቢያ ዋና ከተማ ቤልግሬድ በተካሔደው የዓለም ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቃለች። የቀደሞው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ግዛው ተክለማርያም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። የዛሬው የስፖርት መሠናዶ ይኸን ጨምሮ በሣምንቱ መጨረሻ የተካሔዱ የእግር ኳስ እና የሜዳ ቴኒስ ጨዋታዎችን ይዳስሳል።
በካፍ እገዳ የተጣለበት የአዲስ አበባ ስታዲየም በርካታ እድሳቶች ቢደረጉለትም ሙሉ ለሙሉ አልተጠናቀቀም ። ለመሆኑ ደጋፊዎች ስታዲየሙ ውስጥ ለምን እንዲታደሙ አልተደረገም? የጀርመን ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን በቡድኑ ታሪክ እጅግ ፈጣን በተባለ ግብ የፈረንሳይ አቻውን አሸንፏል ። ሌሎችም፦